ሁሉንም
በአንድ ቃል ለመጠቅለል -ነፍስ በሰውነት ውስጥ እንደምትሆነው ነው፡፡ ነፍስ በሁሉም የሰውነት አካላት ውስጥ አለች፤ ክርስቲያኖችም
እንዲሁ በዓለም ከተሞች ሁሉ አሉ፡፡ ነፍስ በሰውነት ውስጥ ትኖራለች ነገር ግን የሰውነት አይደለችም፤ እንዲሁም ክርስቲያኖች በዓለም
ውስጥ እንዳሉ የታወቀ ነው ነገር ግን ሰማያዊነታቸው ሳይገለጥ ይኖራል፡፡ ሥጋÝ ምንም
እንኳ ደስታን ከማጣጣም በመከልከሏ ጉዳት ባይደርስባትምÝ ነፍስን
ይጠላታል ይዋጋታልም ዓለምምÝ ደስታን በማስወገዳቸው በምንም መልኩ ባይጎዱምÝ
ክርስቲያኖችን
ይጠላቸዋል ፡፡
ነፍስ
የሚጠላትን ሥጋ እንዲሁም አካላቱን ትወዳለች፤ እንዲሁም ክርስቲያኖች የሚጠሏቸውን ይወዷቸዋል፡፡ ነፍስ በሰውነት ውስጥ የታሰረች
ናት ቢሆንም ሰውነትን ትጠብቃለች፤ እንዲሁም ክርስቲያኖች በእስር እንዳሉ ያህል በዓለም ውስጥ ናቸው ቢሆንም እነርሱ የዓለም ታዳጊዎች
ናቸው፡፡ የማትሞተው ነፍስ በሚሞተው ሥጋ ውስጥ ትኖራለች፤ ክርስቲያኖችም በሰማያት የማይጠፋ መኖርያን እየተመለከቱ በሚጠፋ ሰውነት
መጻተኞች ሆነው ይኖራሉ፡፡
ነፍስ
ከመብልና መጠጥ ስትከለከል የበለጠች እየሆነች ትመጣለች፤ ልክ እንደዚሁ ክርስቲያኖች ምንም እንኳ ቀን በቀን ለመከራ ቢዳረጉም በቁጥር
እየበዙ ይሄዳሉ፤ እነርሱ ሊተዉት የማይገባ ይህን የሚታይ ክብር እግዚአብሔር ሰጥቶአቸዋልና፡፡
የማቴተስ መልዕክት ወደ ዲዮግናጠስ /2ኛ መቶዓመት
ግሩም ትምህርት እየሰጠኸን ነው። የታይፕ ስህተቶች ግን ቢስተካከሉ መልካም ነው።
ReplyDelete