ክርስቲያኖች ከሌሎች ሰዎች
ወይ በሀገር ወይ በቋንቋ ወይ በሚያዩዋቸው ልማዶች አይለያዩም። እነርሱ በራሳቸው ከተሞች አይኖሩምና፤ የተለየ የአነጋገር ስልት
አይጠቀሙምና፤ ወጣ ባለ ነገር የሚገለጽ ሕይወትንም አይኖሩምና ፡፡ እነርሱ የሚከተሉት ሥነ ምግባር በማንኛውም ክልስ ሐሳብ ወይ
ጣልቃ ገብ ሰዎች የተቀየሰ አይደለም ፤ጥቂቶች እንደሚያደርጉትም የማንኛውም የሰው ልጅ መመሪያ አስፋፊ አድርገው ራሳቸውን አያስተዋውቁም።
ነገር ግን በግሪክና በባርባር ከተሞች በመኖር እያንዳንዳቸው በተወሰኑበት መሠረት ከአለባበስ ከምግብ እንዲሁም ከተቀሩት መደበኛ
ሥነ ምግባሮች አንጻር የነባር ነዋሪዎችን ልማዶች በመከተል የራሳቸውን አስደናቂና ማራኪ የሆነውን የሕይወት ዘይቤ ይገልጡልናል፡፡
እነርሱ በራሳቸው ከተሞች ይኖራሉ ነገር ግን እንደ ተራ መጻተኞች ሆነው ፡፡ እንደ ዜጎች በሁሉም ነገሮች ከሌሎች ጋር ይጋራሉ ቢሆንም
እንደ ባዕድ ይቸገራሉ፡፡ማንኛውም ባዕድ መሬት ለእነርሱ እንደ እናት መሬት ነው እንዲሁም ማንኛውም የተወለዱበት መሬታቸው ለእነርሱ
እንደ መጻተኞች መሬት ነው፡፡ሌሎች ሁሉ እንደሚያደርጉት እነርሱ ይጋባሉ ልጆችን ይወልዳሉ ዘራቸውን ግን አያጠፉም።የጋራ ጠረጴዛ/ማዕድ
አላቸው የጋራ አልጋ/ርኩሰት ግን የላቸውም፡፡እነርሱ በሥጋ ውስጥ ናቸው ነገር ግን ሥጋን እየተከተሉ አይኖሩም። ቀኖቻቸውን በምድር
ላይ ያሳልፋሉ ነገር ግን እነርሱ የመንግስተ ሰማያት ዜጎች ናቸው፡፡
የተሰጡትን ሕግጋት ይከተላሉ
በተመሳሳይ ጊዜም በሕይወታቸው አብልጠው ይከተሏቸዋል፡፡ሁሉንም ሰዎች ይወዳሉ እንዲሁም በሁሉም ይተቻሉ፡፡እነርሱ ያልታወቁና የተወቀሱ
ናቸው፤ እነርሱ ለሞት የተሰጡ ናቸው እንዲሁም ለሕይወት የተጠበቁ ናቸው፡፡እነርሱ ድሆች ናቸው ቢሆንም ብዙዎችን ባለጠጎች ያደርጋሉ፤
እነርሱ ሁሉን ያጡ ናቸው ቢሆንም ሁሉም የሞላላቸው ናቸው፤እነርሱ የተዋረዱ ናቸው ቢሆንም አብዝተው በተዋረዱ መጠን የተከበሩ ናቸው፡፡እነርሱ
መጥፎ ይነገርባቸዋል ቢሆንም የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡እነርሱ የተጠሉና የተባረኩ ናቸው፡፡እነርሱ የተሰደቡና ስድቡን በበጎ የሚመልሱ
ናቸው፤እነርሱ ጥሩ ያደርጋሉ ቢሆንም እንደ ክፉ ሰሪ ይቀጣሉ።በተቀጡ ጊዜ ወደ ሕይወት እንደሚፈጥን ሰው ደስ ይላቸዋል፤እነርሱ እንደ
ባዕድ በአይሁድ የተጠቁ ናቸው በግሪኮችም የተገፉ ናቸው ቢሆንም እነርሱን የሚጠሉ ለጥላቻቸው ምንም ምክንያት ማቅረብ አይችሉም፡፡
የማቴተስ
መልዕክት ወደ ዲዮግናጠስ /2ኛ
መቶ ዓመት
What an interesting topic, Dn. Yohanes. Thank you for creating this blog and sharing this interesting article with us. It is a very promising beginning.
ReplyDeleteI would recommend you to write about Religion and the Ethiopian Orthodox Church (EOC). Main focus on the importance of a religion and it's background and history in the EOC. Many people especially those abroad would benefits from such kind of articles.
Thanks,
Yonas Tadesse (USA)
MU Alumni
You have started off an interesting blog.
ReplyDeleteKeep it up.
God bless you!!
Please review the comments before they are published.
ReplyDeleteJSTOR Casino: The OG and Greatest Hits! (Live)
ReplyDeleteFrom 강릉 출장마사지 the classic slots to the latest 대전광역 출장샵 releases, the casino 삼척 출장마사지 has hit 광명 출장마사지 the jackpot. Join 순천 출장안마 today to get a chance to win amazing prizes!